ሌሎች ስፖርት

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የዓለም የታዳጊዎች ሜዳ ቴኒስ ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ ቴኒስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የዓለም ታዳጊዎች ሜዳ ቴኒስ ውድድር ተጠናቅቋል።

በውድድሩ ማጠናቀቂያ ስነ ስርዓት ላይ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ  አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ውድድሩ በዘርፉ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እና በስፖርቱ ዘርፍ ዓለም አቀፋዊ ትስስር ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

ከየካቲት 4 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ውድድር የ30 በላይ ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በዕለቱም በሜዳ ቴኒስ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች ሽልማት መበርከቱን ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

አትሌት ሸላቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የኦሜድላ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነ

admin

አስተያየት ይስጡ