ቢዝነስ

ከወጪ ንግድ ከ 1 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

ከወጪ ንግድ ከ 1 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

AMN- ህዳር 17/2016 ዓ.ም

በ2016 በጀት ዓመት 4 ወራት ውሰጥ ከወጪ ንግድ 1.06 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

በአራት ወሩ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጪ በመላክ ገቢ ለማግኘት የተያዘው እቅድ 1.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን አፈፃጸሙ የእቅዱን 65 በመቶ ነው፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ እንደገለጹት የጥራጥሬ ሰብሎች ምርት የእቅዱን 148.5 በመቶ እንዲሁም የቅባት እህሎች 73.4 በመቶ ገቢ በማስገኘት በአራት ወሩ ለተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ሊገኝ የቻለው ላኪዎች የተቀመጡትን የአሰራር ሥርዓቶች ተገንዝበው በመተግበራቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የወጪ ንግዱን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረጉ የውልና ኢንቨስትመንት እርሻ፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሚካሄደው ግብይት፣የወጪ ንግድ ስርዓቱን የማዘመን እና ሌሎችም የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ 4 ወሩ የወጪ ንግድ አፈፃጸም እና በቀጣይ የወጪ ንግዱን በተሻለ መልኩ ለማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከላኪዎች ጋር ውይይት ማካሄዱን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የደብረ ብርሃን ከተማ 24 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጠ

admin

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የሸሪዓ አማካሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

admin

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ነጥብ 4 ቢሊየንብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የለማ መሬት ተላለፈ

admin

አስተያየት ይስጡ