ቢዝነስ

የደብረ ብርሃን ከተማ 24 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 24 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 188 አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ብርሃን ገብረ ሕይወት፥ በማምረት ላይ ያሉ ሥድስት ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ 12 ሚሊየን 529 ሺህ ዶላር ማስገኘት ተችሏል ብለዋል፡፡

በቀጣዩ ግማሽ ዓመትም ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እና 24 ኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲጀምሩ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡

ሳያለሙ ለረዥም ጊዜ መሬት አጥረው የተቀመጡ ባለሃብቶችን በመለየት እርምጃ እንደሚወሰድም ጠቁመዋል፡፡

የውጭና የሀገር ውስጥ አልሚዎችን ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ የመሳብ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወንም ነው አቶ ብርሃን የገለጹት፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

ከወጪ ንግድ ከ 1 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

admin

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የሸሪዓ አማካሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

admin

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ነጥብ 4 ቢሊየንብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የለማ መሬት ተላለፈ

admin

አስተያየት ይስጡ