አትሌቲክስ

በኢትዮጵያ የስኬት ስፖርትን ለማሳደግ ጃፓን ድጋፍ ታደርጋለች: – አምባሳደር ኢቶ ታካኮ

በኢትዮጵያ የስኬት ስፖርትን ለማሳደግ ጃፓን ድጋፍ ታደርጋለች: – አምባሳደር ኢቶ ታካኮ

AMN- ህዳር 17/2016 ዓ.ም

የጃፖን ኤምባሲ ከዪኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ሴት ስኬተሮች የስኬት ቦርድ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በጃፖን የካስማ ከተማ ከንቲባ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ሴት ስፓርተኞች ባላቸው የስፓርት ዝንባሌ ማሳተፍ ለውጤት እንደሚያበቃቸው ገልጸው፤ ድጋፉ በአዲስ አበባ ስፓርቱን ለሚያዘወትሩ ሴት ስኬተርች እንዲውል ከካስማ እሴኬት ፖርክ የተበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው፤ ድጋፉ በዚህ ስጦታ ብቻ የሚቆም ሳይሆን ሴት ስኬተሮች ከካስማ እስኬት ፖርክ ቡድን ጋር ወዳጅነታቸውን በማጠናከር ስፓርቱን ለማሳደግ እና ሴት ስኬተሮችን አቅም ለማሳደግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

የዩኒሴፍ ተወካይ ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነው፤ ድርጅታቸው እንደዚህ አይነት ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል::

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስኬት አሶሴሽን ስፖርቱ በአዲስ አበባ እንዲስፋፋ የሰው ሀይልና በጀት በመመደብ የመወዳደሪያ ቦታዎችን በመገንባት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያስቀጥል በመድረኩ መገለጹን ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

ለ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዝግጅት ላይ የሚገኙ አትሌቶች በወቅታዊ ብቃታቸው የተሻሉ እንደሆኑ ተገለፀ

admin

በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

admin

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በበርሚንግሃም የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አሸነፈች

admin

አስተያየት ይስጡ