አዲስ አበባ

ምግባረ ሰናይ የአረጋውያን፣የአካል ጉዳተኞች እና የህፃናት መርጃ ማእከል ወደ መቄዶኒያ አረጋውያን ማቆያ ማእከልነት ተሸጋገረ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) ሀምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

በሻሻመኔ ከተማ የሚገኘው ምግባረ ሰናይ የአረጋውያን፣የአካል ጉዳተኞች እና የህፃናት ማእከል ወደ መቄዶኒያ አረጋውያን ማቆያ ማእከልነት ተሸጋገረ።

በመርሀግብሩ ላያ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፣ አባ ገዳዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና አረጋዊያን ተገኝተዋል ።

ምግባረ ሰናይ የአረጋውያን፣የአካል ጉዳተኞች እና የህፃናት መረጃ ማእከልን በሻሻመኔ ከተማ የመሰረቱት እማሆይ በለጡ ወ/ሚካኤል የሚባሉ ግብረ ሰናይ ሲሆኑ ዛሬ ላይ እሳቸዉ በህይወት ባይኖሩም በእሳቸዉ የተመሰረተዉ መረዳጃ ማእከል ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋውያንን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና ህፃናትን በአግባቡ እንዲንከባከብ ለመቄዶኒያ አረጋውያን ማቆያ ድርጅት በሙሉ ሃለፊነት ተላልፎ ተሰጥቷል።

በምግባረ ሰናይ የአረጋውያን፣የአካል ጉዳተኞች እና የህፃናት መረጃ ማእከል ያነጋገርናቸዉ ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋውያንን ፣ አካል ጉዳተኞችም በተለያዩ ቦታዎች ደጋፊ ያጡ ዜጎች መጠለያና እገዛ እንዲያገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ሊተባበሩ ይገባል ብለዋል።

ሰዉ ለመርዳት ሰዉ መሆን ብቻ በቂ ነዉ በሚለዉ መሪ ቃል የሚታወቀዉ መቄዶንያ የአረጋውያን ማቆያ ማእከል በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ቅርንጫፍ ማእከላት ያሉት ሲሆን በዛሬዉ እለትም በሻሻመኔ ከተማ እንደ አዲስ ቅርንጫፍ የተከፈተው ማእከልም በርካታ ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋውያንን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና ህፃናትን ሰብስቦ በአግባቡ እንደሚንከባከብ ተስፋ ተጥሎበታል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ