አዲስ አበባ

በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ግንዛቤን በመፍጠር’ ብልሹ አሰራርን በመከላከል እና ተጠያቂነትን በማስፈን ገቢን ለማሳደግ ይሰራል፡-የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ግንዛቤን በመፍጠር’ ብልሹ አሰራርን በመከላከል እና ተጠያቂነትን በማስፈን ገቢን ለማሳደግ ይሰራል፡-የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መጋቢት 10/2015 ዓ.ም

በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ግንዛቤን በመፍጠር’ ብልሹ አሰራርን በመከላከል እና ተጠያቂነትን በማስፈን ገቢን ለማሳደግ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ገለጹ፡፡

’’ግብር ለሀገር ክብር’’ የግብር ንቅናቄና የሽልማትና የእውቅና መርሀግብር በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል፡፡

የንቅንቃኔ መድረኩ ዋና አላማ አዲስ አበባን በቀጣይ የልማትና የብልጽግና ማእከል በማድረግ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ቀጣይነት ማረጋገጥ ነው ያሉት የቢሮ ኃላፊው በግብር ከፋይነት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት እውቅናና ሽልማት በመስጠት ማበረታታት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ህብረተሰቡን በማሳተፍ በፍቃደኝነት ግብር የመክፈልባህልን በማሳደግ ለንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር ቁጥራቸውን መጨመር እና የተሻ አገለግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ሌላው የመርሀግብሩ አላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ዘንድ የህግ ተገዢነትን በማስፈን ግብረ ከፋዩን ማበረታታትም የመድረኩ ሌላው አላማ እንደሆነ አቶ አደም ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ በአዲስ አበባ 56 ሺ 745 ግብራቸውን የሚያሳዉቁ ግብር ከፋዮች መኖራቸውን ያወሱ ኃላፊው እነዚህም በከፍተኛ ‘መካከለኛ እና ዝቅተኛ የህግ ተገዢነት ግብር ከፋዮች በሚል መከፈላቸውን ያወሱት አቶ ኑሪ እነዚህ የህብረተሰብ ክፈሎች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ በቢሮው ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡

ዛሬ ተሸላሚ በመሆን እውቅና ያገኙት 300 ግብር ከፋዮች የንግድ አድራሻቸውን እና’የባንክ ሂሳባቸውን ያሳወቁ ቅጣት የሌለባቸው’ ከሽያጫቸው ላይ ትክክለኛውን ገቢ የሚከፍሉ ‘ከስወራ ጋር በተያያዘ ምንም ወንጀል የሌለባቸው ታማኝ ግብር ከፋዮች ናቸው ብለዋል፡፡

ከእነዚህ 300 ታማኝ ግብር ከፋዮች 73ቱ ሴቶች መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ኑሪ እነዚህ ግብር ከፋዮች በቀጣይ ቅድሚ አገልግሎት የሚያገኙበት ልዩ ካርድ እንደሚሰጣቸውም ተናግረዋል፡፡

ዛሬም በአዲስ አበባ ከፍተኛ የልማት ፍላጎት እንዳለ ያነሱት የቢሮ ኃላፊው የምታገኘው ገቢም እየጨመረ ቢመጣም አሁን በቂ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡

የንግዱ ህብረተሰብ በህግ በተደነገገው መሰረት ግብሩን እንዲከፍል እንደሚሰራ የገለጹት አቶ አደም በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ግንዛቤን በመፍጠር’ ብልሹ አሰራርን በመከላከል እና ተጠያቂነትን በማስፈን ገቢን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በመርሀግብሩ ለእውቅናና ሽልማት ከበቁ 300 የንግዱ ማህበረሰብ ውስጥ 49ኙ በፕላቲኒየም ‘101ዱ በወርቅ’እንዲሁን 150 ዎቹ በብር ደረጃ ተሸላሚ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

3ቱ ልዩ ተሸላሚመሆናቸውም ተወስቷል፡፡

አድራሻን’ የንግድ ዘርፍን’ ህጋዊ የባንክ ደብተርን ያሳወቁ ‘ቅጣት የሌለባቸው’ የኦዲት ግኝትም ሆነ ልዩነት ያልተገኘባቸው’መክፈል የሚገባቸውን ግብር በወቅቱና በአግባቡ የከፈሉ’የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያን በትክክልና በአግባቡ የሚጠቀሙ መሆናቸው ለሽልማቱ ያበቋቸው መስፈርቶች መሆናቸው በመርሀግብሩ ላይ ተመልክቷል፡፡

አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ የአዲስ አበባ የታክስ አምባሳደር በመሆን ተመርጣለች፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ