አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ትናንት ማምሻዉን በደረሱ ሶስት የእሳት አደጋዎች በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል

ትናንት ማምሻዉን በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ ሶስት የእሳት አደጋዎች በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም

የኮሚሸኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ባደረሱን መረጃ የመጀሪያው አደጋ ያጋጠመው ትናንት ማምሻዉን 11:26 ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አደይ አበባ አካባቢ በሁለት ሆቴሎችና በአንድ ፔንሲዮን ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ሲሆን በዚህም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት፡፡

ሁለተኛዉ አደጋ ያጋጠመዉ ከምሽት 12:20 ሰዓት ላይ በንፋሰ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በአንድ ባጃጅ ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ሲሆን ባጃጇ ሙሉ በሙሉ መቃጠሏን አቶ ንጋቱ ገልፀዋል፡፡

ሶስተኛዉ አደጋ የደረሰው ከምሽት 3:05 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ዘነበ ወርቅ ባጃጅ ተራ ሲሆን በዚህ የእሳት አደጋም የተለያዩ የንግድ አገልግሎት የሚሰጥባቸዉ 6 የንግድ ቤቶች ተቃጥለዋል ነው ያሉት፡፡

የደረሱትን የእሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር 13 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ፣ሁለት አምቡላንሶችና 78 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋው ተዛምቶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ መቻሉን አቶ ንጋቱ አመላክተዋል፡፡

ሶስቱንም የእሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር አምስት ሰዓት የፈጀ ሲሆን በደረሱት የእሳት አደጋዎች በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ