አዲስ አበባ

በክረምት ወቅት የሚከሰት የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ የድሬኔጅ መስመሮች ጥገና እና ፅዳት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ

በክረምት ወቅት የሚከሰት የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ የድሬኔጅ መስመሮች ጥገና እና ፅዳት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በአፈር፣ በቆሻሻና መሰል ምክንያቶች የተደፈኑ እና ለብልሽት የተዳረጉ የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮችን በመለየት የፅዳት እና የጥገና ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በክረምት ወቅት በውሃ መፋሰሻ መስመሮች መደፈን ምክንያት የጎርፍ አደጋ ስጋት ከመከሰቱም ባሻገር መንገዶችም ለብልሽት እንደሚዳርግ ተገልጿል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ችግር ለመቅረፍ የድሬኔጅ መስመር ጥገና እና ፅዳት ስራ በበጋው ወቅት በስፋት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሷል፡፡

በዚህም መሰረት እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ 111.9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የድሬነጅ መስመር የፅዳት እና የጥገና ስራ መከናወኑን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ በቁጥር 1274 የማንሆል ክዳኖችን በመቀየር ለአገልግሎት መብቃቱ ተመላክቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለማከናወን በዕቅድ ከያዛቸው የድሬኔጅ ፅዳትና ጥገና ሥራዎች በተጨማሪም ከእሳት እና ድንገተኛ ስራ አመራር ኮሚሽን የሚመጡ ጥቆማዎችን ጨምሮ የጎርፍ አደጋ ስጋት አካባቢዎችን አካቶ እየሰራ እንደሚገኝ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ