አዲስ አበባ

ባለፉት ሰባት ወራት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ

ባለፉት ሰባት ወራት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መጋቢት 10/2015 ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገቢ ማሰባሳቢያ የ6ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄዷል።

“የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን የብሄራዊ ጽናት ምልክታችን!!” በሚል መሪ ቃል ለግድቡ ግንባታ የገቢ ማሰባሳቢያ የ6ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ታዋቂ አትሌቶች ፥ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተከናወኗል።

በመርሃ ግብሩ የቦንድና ቲሸርት ሽያጭ በተጨማሪ በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ተከናውነዋል።

በሩጫው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ብሩክ ከድር የዛሬው ሩጫ ዋና ዓላማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ 12ኛ ዓመት የምስረታ ቀንን ማክበር፣ 4ኛዉ ዙር የውሃ ሙሌትን በስኬት ማጠናቀና ግድቡን በፋይናንስ መደገፍ ዓላማዉ አድርጎ የተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

ባለፉት ሰባት ወራት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድባችን የነጻነት አርማችንና በራሳችን አቅም መለወጥ እንደምንችል ማረጋገጫችን ነው ያሉት ዶክተር ብሩክ በዚህ ሂደት ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የነበሩትን የክፍለ ከተማውንና የከተማዋን ነዋሪዎች አመስግነዋል።

ግድብ እስኪጠናቀቅም ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት መስክ ሁሉ በገንዘብና ባለው እውቀት ሁሉ እንዲደግፍም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ያለምንም እርዳታ ያለምንም ብድር በሀገራችን የልማት አርበኛ በሆነው ህዝባችንና መንግስታችን የጋራ ትብብር የምንገነባው በመሆኑ ታላቅ ክብር ሊሰማን ይገባል ብለዋል።

“ለህዳሴው ሩጫ በቂርቆስ” በተሰኘው የሩጫ መርሐ ግብር አትሌት ስለሺ ስህንን እና አትሌት ፋንቱ ነጌሶ መሳተፋቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ