አዲስ አበባ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተደራሽነቱን በማስፋት የህዝብ ድምጽነቱን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተደራሽነቱን በማስፋት የህዝብ ድምጽነቱን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ፡፡አዲስ ሚዲያኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 1/2015 ዓም

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሰራተኞች የተቋሙን ያለፉ ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም እና የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ተቋሙ ባለፉት ስድት ወራት ተደራሽነቱን ለማስፋትና የህዝብ ድምጽ ለመሆን ያደረገው ጥረት አበረታች መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ አሁን የጀመረውን የለውጥ ሂደት ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል የሜትሮፖሊታን ሚዲያነቱን ማስፋ ይገባዋል ብለዋል፡፡

ተቋሙ በቀጣይ የከተማውን ነዋሪ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በመስራት የህዝብ ድምጽ ለመሆን ተግቶ ይሰራልም ብለዋል፡፡

ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸው ተግባራት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ጠንካራ ተግባራትን ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠልና ቀሪ ተግባራትን በቀጣይ በተሻለ ለማከናወን ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተደራሽነቱን በማስፋት የህዝብ ሚዲያነቱን በተሻለ ለማከናወን ሰራተኛውና ተቋሙ ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸውም ተመላክቷል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ