አዲስ አበባ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’መደመር ትዉልድ’ መጽሐፍ ገቢ ለህፃናት መዋያና መጫወቻ ስፍራ መገንቢያ እንዲዉል ስላበረከቱ ምስጋና አቀረቡ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’መደመር ትዉልድ’ መጽሐፍ ገቢ ለህፃናት መዋያና መጫወቻ ስፍራ መገንቢያ እንዲዉል ስላበረከቱ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መጋቢት 9/2015 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስአበባ የሚሸጠውን የ’መደመር ትዉልድ’ መጽሐፍ ገቢ ለከተማዋ ህፃናት መዋያና መጫወቻ ስፍራ መገንቢያ እንዲዉል በማበርከታቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ነዋሪዎች ስም ምስጋና አቀረቡ።

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “የከተማችን ነዋሪዎች ይህንን መጽሐፍ በመግዛት ለልጆቻችሁ የመጫወቻና መዋያ ቦታ መገንባት እንድንችል እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመደመር ትውልድ መጽሐፍ በሀሳብም በገንዘብም ትውልድ የሚሰራ በመሆኑ ክልሎች ከመጽሐፉ ሽያጭ ያገኙትን ገንዘብ የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመገንባትና ቅርሶችን ለማደስ እንዲጠቀሙበትም በስጦታ አበርክተዋል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ