አዲስ አበባ

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ህዳር 2/2016 ዓ.ም

ዛሬ የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ:

“በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ከገነባናቸው ሆስፒታሎች ሁሉ የሚልቁት የቤተል-መንዲዳ ሪፈራል ሆስፒታል እና የላፍቶ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታቸው በተያዘው በጀት አመት ሲጠናቀቁ ከሚሰጡት ማህበራዊ ፋይዳ በተጨማሪ ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጉ ይሆናል” ሲሉ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልፀዋል ::

“በከተማችን ያለውን የቤት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ በከተማው በጀት ግንባታቸው የተጀመሩ የ5000 ቤቶች ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶችን ውስጥ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ 400 ቤቶችን አይተናል” ሲሉም አመልክተዋል ::

“ለከተማችን 4ኛው የገበያ ማዕከል የሆነው የላፍቶ ምዕራፍ 2 የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል 144 ሱቆች እና 14 መጋዘኖች የተካተቱበት ሲሆን በቀጣይ 90 ቀናት ውስጥ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የገበያ ሰንሰለቱን በማስተካከል አምራችን በቀጥታ ከሸማች ጋር በማገናኘት የአዲስ አበባን ህዝብ የኑሮ ጫና የማቃለል ስራችንን ውጤታማ የሚያደርግ ይሆናል” ብለዋል ::

“አዲስ አበባን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ ማድረግ በቃል ብቻ ሳይሆን የገባነው ቃል በተግባር እውን እየሆነ በመምጣቱ እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል ::

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

በቴክኔክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆቻችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናችውን 6244 ተመራቂዎች ዛሬ አስመርቀናል” ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

admin

አስተያየት ይስጡ