አዲስ አበባ

“የህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው የቤት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የ100,000 ቤቶች ለመገንባት ከአልሚዎች ጋር ዛሬ ተፈራርመናል”-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው የቤት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የ100,000 ቤቶች ለመገንባት ከአልሚዎች ጋር ዛሬ ተፈራርመናል”-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ( ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም

የህዝቡ አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው የቤት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የ100,000 ቤቶች ግንባታን በመንግስት እና የግል አጋርነት በ70/30 መርሃ ግብር ለመገንባት ከአልሚዎች ጋር ዛሬ መፈራረማቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

“በከተማችን ያለውን የቤት አቅርቦት እጥረት መንግስት ለብቻው የሚፈታው ባለመሆኑ፣ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማሳተፍ መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ይህ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ህዝባችንን ለማገልገል የገባነውን ቃል በማክበር የህዝቡን ችግር ለሚቀርፉ ስራዎች ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ለመሆኑ ማሳያ ነው” ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት።

“የከተማችንን ነዋሪዎች መሰረታዊ ጥያቄ ለመመለስ ከገንዘብ ትርፋችሁ አስበልጣችሁ የህዝባችሁን ጥያቄ ለመመለስ ምላሽ የሰጣችሁን የከተማችን ባለሃብቶችን በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” ብለዋል ከንቲባዋ።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ