አዲስ አበባ

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ለዴሞክራሲና ለሰላም ግንባታ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ለዴሞክራሲና ለሰላም ግንባታ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 29/2015 ዓ.ም
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ለዴሞክራሲና ለሰላም ግንባታ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ።

የመገናኛ ብዙኃን ለሀገራዊ ጥቅም ያላቸውን ሚና የሚዳስስ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ለብሔራዊ ጥቅም ፣ ለዴሞክራሲና ለሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ብዝሃነትን፣ ሠላም እና አንድነትን ከማስጠበቅ አንፃር ልዩ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ ኢዜአ በ2022 የአፍሪካ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ለመሆን የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ “መገናኛ ብዙሃን አና ሀገራዊ ጥቅም” “መገናኛ ብዙሃንና ዴሞክራሲ” እንዲሁም “መገናኛ ብዙሃንና ሰላም” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት መነሻ ሃሳብ በተለያዩ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በካሳሁን አንዷለም

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ