አዲስ አበባ

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በፓርቲው የስድስት ወር አፈፃፀም ላይ ሲያካሂዱት የነበረውን ውይይት አጠናቀቁ፡፡

በመድረኩ ላይ የፓርቲውን የውስጠ ዴሞክራሲ ባህል በማሳደግ በቀጣይ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ትግል በማድረግ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማስፋት እንዲሁም ድክመቶችን አርሞ በመሄድ ረገድ ሰፊ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቅሷል።

የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎችን በአግባቡ መከወን የሚያስችል መዋቅር በማጠናከር ከዋና ጽ/ቤት እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ድረስ የተሰናሰለ የተግባር አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል ከፍተኛ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

የብልፅግና ፓርቲን መርሆች፣ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎችን ወደ ህብረተሰቡ በተቀናጀ መልኩ በማስረፅ በመደመር እሳቤ የተዋጀ የብልፅግና መንገድ መፍጠር ትልቁ የቤት ስራ እንደሆነ በመገንዘብ ቀጣይ የርብርብ ማእከል መሆን እንደሚገባውም መግባባት ላይ ተደርሷል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ