አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበለትን የምክር ቤት ጽ/ቤቱ ማሻሻያ ረቀቂ አዋጅ አጽድቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበለትን የምክር ቤት ጽ/ቤቱ ማሻሻያ ረቀቂ አዋጅ አጽድቋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበለትን የምክር ቤት ጽ/ቤቱ ማሻሻያ ረቀቂ አዋጅ አጽድቋል፡፡

የከተማዋ ምክር ቤቱ ከተመለከታቸወ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ይገኝበታል፡፡

ምክር ቤቱ ለመረጠው ህዝብ ድምጽ መሆን እዲችል የምክር ቤቱ ጽ/ቤት አስላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ጠንካራ አደረጃጀት ሊኖረው ይገባል ተብሎ በመታመኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሰላምና ፍትህ አስተዳዳር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ከዚህ በፊት የነበረዉ አዋጅ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤቱ ጽ/ቤት አዋጅ መሻሻል ምክር ቤቱ የበለጠ አቅም እንዲኖረዉ እና ከህዝብ የተሰጠዉን አደራ በተግባር ለመወጣት ፋይዳዉ የጎላ መሆኑንም አቶ ሙሉነህ ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ የምክር ቤት አባላት ከተወያዩ በኋላም ጸድቋል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ