አዲስ አበባ

የዜጎችን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ይበልጥ ለመመለስና ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ የንብረት ገቢ ግብርን አሟጦ መጠቀም ይገባል-ረዳት ፕሮፌሰር ሙሴ በየነ

የዜጎችን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ይበልጥ ለመመለስና ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ የንብረት ገቢ ግብርን አሟጦ መጠቀም ይገባል-ረዳት ፕሮፌሰር ሙሴ በየነ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ግንቦት 01/2015 ዓ.ም
የዜጎችን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ይበልጥ ለመመለስና ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ የንብረት ገቢ ግብርን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ የፋይናንሰ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ሙሴ በየነ ገለጹ፡፡

ረዳት ፕሮፌሰር ሙሴ በየነ የንብረት ገቢ ግብርን በተመለከተ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ የንብረት ገቢ ግብር ባደጉት ሀገራት ከዘመናት በፊት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም አሜሪካ በ17ኛው ክፍለዘመን የንብረት ገቢ ግብር በመሬት ላይ ጀምራ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረት ግብሮችን በማከል የከተሞቿን ሁለንተናዊ እድገት ከንብረት ገቢ ግብር እንደምትሸፍን ነው የጠቆሙት፡፡

በአህጉረ አፍሪካም አፈጻጸሙና አተገባበሩ ከሀገር ሀገር ቢለያይም ከመስኩ የተሻለ ገቢ ከሚያገኙ በርካታ ሀገራት መካከል ጎረቤት ሀገር ኬንያ አንዷ መሆኗን ረዳት ፕሮፌሰሩ አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሁሉ ከ60 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የንብረት ህግን ገቢራዊ አድርጎ ከመስኩ የሚገኘውን መጠቀም ላይ ሰፊ ክፍተት መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

ይህ በመሆኑም ለከተሞች የላቀ እድገት ውስንነት፤ የበጀት ጉድለት እና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት መጓደል ተጨማሪ ምክንያት መሆኑን ነው ምሁሩ የጠቆሙት፡፡

መንግስት አሁን ላይ የገቢ ግብርን ተፈጻሚ ለማድረግ መነሳሳቱ ከህልውና መሰረት ጋር የሚያያዝ ወቅታዊ ጉዳይ ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ሙሴ አንድም በከተሞች ብሎም እንደሀገር እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ታሳቢ ያደረገ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

መሰረተ ልማትን ለማሟላት እና የከተሞች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የንብረት ገቢ ግብርን ተፈጻሚ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ይህም በተዘዋዋሪ ለዜጎች መሰረታዊ ፍላጎት ጭምር እንደሚውልና እና የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የገቢ ግብርን ተግባራዊ ማድረግ እንደ ሀገር በተለይም እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገ የሚባል አይደለም ያሉት ምሁሩ የገቢ ምንጮችን ማስፋት እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግስት ወጪዎችን መቀነስም ጎን ለጎን ተጣጥሞ መሄድ እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

የንብረት ገቢ ህግን ይበልጥ ተፈጻሚ ለማድረግ ከዘመናዊ እስከ ፍትሐዊ አሰራር ድረስ በአግባቡ ሊተገበር እንደሚገባም ምክረ ሃሳባቸዉን አጋርተዋል፡፡

በኤልያስ ተክለወልድ

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ