ኢትዮጵያ

መንግስት ከሸኔ ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

መንግስት ከሸኔ ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መጋቢት 19/2015
መንግስት ከሸኔ ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ እየሰጡ ነው፡፡

ሸኔን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፤ ችግሩን ለመፍታት ባለፉት ጊዜያት ከአስር በላይ ንግግሮች መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም የተደረገው የሰላም ጥሪ እንደፓርቲ በመነጋገር የተወሰነ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ጥሪው የዚሁ ንግግር ተቀጥያ ነውም ብለዋል።

ነገር ግን ቡድኑ አንድ የተሰባሰበ ሀይል ስላልሆነ ችግር መፍጠሩን ተናግረዋል።

መንግስት ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንና ይበልጥ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ እና ለመከላከል የጸጥታ ሃይሉ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ