ኢትዮጵያ

ሰብአዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በተለያየ መንገድ ማገዝ ይገባል-አቶ ጌታቸው ረዳ

ሰብአዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በተለያየ መንገድ ማገዝ ይገባል-አቶ ጌታቸው ረዳ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ህዳር 2 /2016 ዓ.ም

በሰብአዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በተለያየ መንገድ ማገዝ እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አረጋውያን፣ ሕጻናትና የአዕምሮ ሕሙማንን ለማገዝ ያለመ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዛሬ በመቀሌ ከተማ ተካሂዷል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ውድድሩን ሲያስጀምሩ ለከፋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን ማገዝ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የፍሬምናጦስ የአረጋውያን፣ የህጻናትና የአዕምሮ ሕሙማን ማገገሚያ ማዕከል ለእነዚህ ወገኖች እያደረገ ያለውን ድጋፍ በአርአያነት መከተል እንደሚገባም ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በሰብአዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን እያገዘ መሆኑን ጠቅሰው ስኬቱን ይበልጥ ለማሳደግ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

የፍሬምናጦስ ማገገሚያ ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አባ ገብረመድህን በርኸ በበኩላቸው ከ300 በላይ አረጋውያንና ህጻናት በማዕከሉ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

በቀጣይ ሁለት ዓመት ውስጥም ማዕከሉ በተሰጠው 43 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ከ2ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ማገገሚያ ማዕከል በ3 ቢሊዮን ብር ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።

ለማዕከሉ ግንባታ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ የተካሄደውን የጎዳና ላይ ሩጫ ፍሬምናጦስ ማገገሚያ ማዕከል ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና ስፖትር ኮሚሽን ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት ታውቋል።

ከሩጫ ውድድሩ የተገኘው ገቢም ለማዕከሉ ግንባታ እንደሚውል የማዕከሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።

በሩጫው የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎችም የተቸገሩ ወገኖችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ዛሬ በመቀሌ ከተማ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በውድድር ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁና ለዝግጅቱ ጥሩ ተሳትፎ ላደረጉ አካላት የማበረታቻ ሽልማቶች መበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ