ኢትዮጵያ

ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ቀን ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 ስድስተኛው ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ÷ በስልጠናው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ከ15 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

በጎ ፈቃደኞቹ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በመሰማራት በተለያዩ ዘርፎች ነጻ አገልግሎት እንደሚሰጡ አመላክተዋል።

የበጎ ፈቃድ ስልጠናው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን÷ በስራ ፈጠራ፣ ስነ ልቦና እና ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።

ባህር ዳር፣ ጅማ፣ ዋቻሞ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናው የሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ