ኢትዮጵያ

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

AMN- ህዳር 17/2016 ዓ.ም

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ ዘጠኝ ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ነገ እና ከነገ በስቲያ ለሚካሄደው 32ኛው የትምህርት ጉባኤ የቅድመ ጉባኤ ምክክር በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት ይገባቸዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የተሻሉ፣ በምርምር የጎለበቱ እና በሥነ-ምግባር የታነጹ ዜጎችን ለመፍጠርም በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታትም በተልዕኮና በትኩረት መስካቸው የተለዩ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

እነዚህም ሁለት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም ሰባት የምርምር ዩኒቨርስቲዎች ናቸው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

የ32ኛው ጉባዔ ዋና ዓላማም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ላጋጠሙ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን ለማበጀት ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የራስ ገዝነት ተስፋና ተግዳሮት በሚል ጽሑፋቸው ዩኒቨርስቲዎች ለዚህ መዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑ ይተወቃል።

እየተካሄደ በሚገኘው መርሃ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ፣ የክልል የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ሌሎችም እየተሳተፉበት ነው።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ስምሪት አደረገ፡፡

admin

አስተያየት ይስጡ