ኢትዮጵያ

በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህትማማቾች 7 ሺሕ መጻህፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለገሱ

በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህትማማቾች 7 ሺሕ መጻህፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለገሱ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 29/2015 ዓ.ም
በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህትማማች በትውልድ ኢትዮጵየውያን ወጣቶች ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ያሰባሰቡትን 7ሺህ መጽሐፍትን ለኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረክበዋል።

ወ/ሮ አያንቱ አበበ በልጆቻቸው በኩል የተሰበሰቡትን መጽሃፍትን ለኤምባሲው አስረክበዋል። ልጆቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዲኖራቸው ለማድረግና የበጎ ስራ አርዓያ እንዲሆኑ ይህ መጽሃፍትን የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን አውስተዋል።

የተለገሱት መጻህፍት በኢትዮጵያ የንባብ ባህል፣ እንዲዳብር ቤተ መጻህፍት የተሟላ አቅርቦት እንዲኖራቸው ለማገዝ ነው።

የተለገሱት መጻህፍት ቋንቋ፣ ስነ- ህይዎት፣ የታሪክ፣ የሂሳብ፣ የምርመርና ሌሎች ጠቃሚ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ እንደሆኑ ሁለቱ እህታማማቾች ገልጸዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ፣ ይህን መሰል ትውልድን የሚያንጹ መጽሃፍት በመለገስ ለተደረገው አርዓያነት ያለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

መጽሃፍቶቹም ከሌሎች መሰል የዳያስፖራ ወገኖች ከተለገሷቸው ጋር በመሆን ለአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የሚላኩ መሆናቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ