ኢትዮጵያ

በዱብቲ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 3 ልጆችን ተገላገሉ

በዱብቲ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 3 ልጆችን ተገላገሉ

AMN-ህዳር 01/2016 ዓ.ም

በአፋር ክልል ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ወንዶች ልጆችንና አንዲት ሴት ልጅ በአንድ ጊዜ ተገላግለዋል።

ከሆስፒታሉ ማህጸንና ጽንስ ክፍል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ህጻናቱ 2.7 ፣ 2.6 እና 2.5 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ።

እናት ወ/ሮ ኡንዳኬ አቡበከር ከኤሊዳር ወረዳ በሪፈር መምጣታቸውና በቀዶ ህክምና ሶስቱን ልጆች መገላገላቸው ታውቋል ።

ህጻናቱም ይሁኑ እናትየው በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ከዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ