ኢትዮጵያ

“አሁን የሚያስፈልገን ሰይፍ የሰላም፤የፍቅር እና የይቅርታ ሰይፍ ነው”-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

“አሁን የሚያስፈልገን ሰይፍ የሰላም፤የፍቅር እና የይቅርታ ሰይፍ ነው”-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መጋቢት 19/2015
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽና ማብራርያ እየሰጡ ነው፡፡

ሰላምን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራርያ አሁን ላይ በሀገሪቱ ከዛሬ 6 ወር የተሻለ የሰላም ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ሰላም አንጻራዊ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ስራዎች ይጠበቁብናል ብለዋል፡፡

ጦርነት እንደቆመ ወዲያውኑ ሰላም አይሰፍንም ድኅረ ጦርነት አውድ ጫና አለ ሲሉም ተናግረዋል።

ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ፖለቲካ የመተላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውሰዋል፡፡

ጦርነት የሚጎስሙ ሃይሎች ጦርነትን የሚያውቁ አይደሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ሃይሎች ግጭት ለመፍጠር ቀድመው ያቅዳሉ፤ ግጭት ይፈበርካሉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራርያቸው አሁን የሚያስፈልገን ሰይፍ የሰላም፤ የፍቅር እና የይቅርታ መሆን አለበት ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ሰላምን ማምጣት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ ሰላም እንደ ጦርነት ጀግንነትን ይፈልጋል: ከጦርነት ያልተናነሰ ሥራ፣ ድካም ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ለጦርነት በቀላሉ ሰዎችን ማሰባሰብ ይቻላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰላም መዝመት ግን ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡

የሚሻለውን ነገር ለማምጣት ከኛ ይቅር በማለት አዎንታዊ ሰላም ለማምጣት አብረን እንትጋ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተሟላ ሰላም ለማምጣት የሚያስፈልጉ የንግግር፣ የምክክር፣ የመተማመን ስራዎች በስፋት መጀመራቸውን በመጥቀስ እነዚህ ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉም ነው ያሉት፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ