ኢትዮጵያ

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ ከቤልጂየም አምባሳደርና ከእንግሊዝ የልማት ትብብር ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ.ኤም.ኤን) የካቲት 22/2015 ዓ.ም

ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ የቤልጂዬም አምባሳደር እና ከኢንግሊዝ የልማት ትብብር ዳይሬክተር ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ በምክክሩ በኮሚሽኑ ዓላማዎችና ፕሮግራም ላይ መሰረት ያደረጉ ዋና ዋና ግቦች እና በተልዕኮው ስኬት የልማት አጋሮችን ሚና በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በምክክሩም በኢትዮጵያ የቤልጂዬም አምባሳደር ሚስ ክራ ስንድበጀርግ እና አንደኛ ጸሃፊ ሚስ ትሪኒ ሊውስ ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከኢንግሊዝ ኤምባሲም የልማት ትብብር ዳይሬክተር ሚስተር ፓውል ዋልተር እና የሰላምና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ቡድን መሪ ዳን ሲልበርም ተሳታፊ ነበሩ።

በምክክሩ ሁለቱ አገራት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጅምሮችና የተሃድሶ ኮሚሽን በተለይም በሰላም ስምምነቱ መሰረት መልሶ ለማቋቋምና የሰላምና የልማት አካል ለማድረግ የሚያደረገውን እንቅስቃሴ የሚደግፉ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ