ኢትዮጵያ

አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28 ፣ 2015 አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን÷ ‹‹የሥነ ጽሑፍ መሰረታውያን›› እና ‹‹ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ›› የሚሉትን ለሥነ ጽሑፍ ትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ጨምሮ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን አሳትመዋል፡፡

ምሁሩ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ መምህርነት እና አማካሪነት እያገለገሉ እንደነበር የሙያ ባልደረቦቻቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በቅርቡም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሰውመሆን ፊልሞች ጋር በመተባበር ለሚሰራው “ፍቅር እስከ መቃብር ” ባለ 48 ክፍል የቴሌቪዥን ድራማ ሙያዊ ሀሳባቸውን ማካፈላቸው ይታወቃል፡፡

AMN ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ