ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸውን የረዥም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ መጠቀም የሚችሉበት ጸጋና ዕድል አላቸው- አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ

ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸውን የረዥም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ መጠቀም የሚችሉበት ጸጋና ዕድል አላቸው- አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) ሀምሌ 22/2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸውን የረዥም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ መጠቀም የሚችሉበት ጸጋና ዕድል እንዳላቸው የቀድሞው ዲፕሎማት አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያና የሩሲያ ግንኙነት 125 ዓመታት እድሜ ያስቆጠረ መሆኑን በሩሲያ የኢትዮጵያ እንደራሴ ሆነው ያገለገሉት የቀድሞ ዲፕሎማት አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ይህ የረዥም ዘመን ግንኙነት ታሪካዊ መሆኑንም አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ የኢትዮጵያ ሁልጊዜ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ያነሱት አምባሳደር አለማየሁ ሩሲያ ኢትዮጵያ ችግር ባጋጠመት ጊዜ ከኢትዮጵያ ጎን የቆመች እውነተኛ ወዳጅ መሆኗን አንስተዋል፡፡

በዘመን መተካካትና በጊዜ መደራረብ ያልደበዘዘው የሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት አሁንም ድረስ በመተማመን፡በመተሳሰብ እና ብሄራዊ ጥቅምን ባከበረ የግንኙነት መርህ የዘለቀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሩሲያ የህዳሴ ግድብ ፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነትን በተመለከተ ትክክለኛ አቋም ይዛ በአለም አቀፍ ደረጃ አቋሟን ስታራምድ የነበረ እና የአፍሪካ ችግር በአፍረካዊ መፍትሄ በማለት ከኢትዮጵያ ጎን የቆመች ሀገር መሆኗንም ነው አምባሳደሩ ያስታወሱት፡፡

ከረዥሙና ታሪካዊው ከኢትዮጵያና የሩሲያ ግንኙነት ሀገራቱ ይበልጥ መጠቀም የሚችሉት ጸጋና እድል እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

የጠነከረውን የባህልና ማህበራዊ ዘርፍ ትብብር በኢኮኖሚው መስክም ለማጎልበት ጅማሮዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሩሲያ ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝትና ብሄራዊ ጥቅምን ማረጋገጥ የሚችሉ ምክክሮች ለታሪካዊው የኢትዮጵያና ሩሲያ ግንኙነት ይበልጥ ትርጉምና እሴት እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሩሲያ አሁንም በሀገራት ጉዳይ ጣልቃ ባለመግባት መርህ እንዲሁም የመተባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የትብብር አማራጭ ለአፍሪካ ተስፋን የምትሞላ አጋር እንደሆነች አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ተናግረዋል፡፡

በአቡ ቻሌ

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ