ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

AMN- ህዳር 17/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች የቢክ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለሚፈጥሩ ጥቃቅን; አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በሚያቀርበው የብድር አገልግሎት እንዲሁም የባንክ ተጠቃሚ ላልነበሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎትን በማዳረስ እና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና የገንዘብ ብድር አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን አሰራር እየዘረጋ በመሆኑ የዘንድሮውን የቢክ ኢትዮጵያ አሸናፊ በመሆን የእውቅና ሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

ቢክ ኢትዮጵያ የቢክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ሲሆን በስራ ፈጠራ ላይ ለተሰማሩ እና የስራ እድል ለሚፈጥሩ ተቋማት ክህሎትን በማጋራት አፍሪካ ከአውሮፓ ጋር የተቀላጠፈ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትስስር እንዲኖር የሚረዳ ተቋም ነው።

ቢክ አፍሪካ በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ላይ ልማትን በሚያፋጥኑ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ የሚሰራ በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ስምሪት አደረገ፡፡

admin

አስተያየት ይስጡ