ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና በዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መከሩ

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና በዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል።

በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ ያሉ የአፈጻጸም ሂደቶች፣ በልማት እና በዴሞክራሲ ግንባታ በሚሰሯቸው ስራዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ ሁለቱ ሃገራት መምከራቸውንም ገልፀዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ