ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ከውሃ ሀብቷ የበለጠ እንድትጠቀም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተጠቆመ

ኢትዮጵያ ከውሃ ሀብቷ የበለጠ እንድትጠቀም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተጠቆመ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 29/2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ከውሃ ሀብቷ የበለጠ እንድትጠቀም ሳይንሳዊ ምርምሮችን ለማድረግ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተጠቆመ።

8ኛው የውሃ ዲፕሎማሲ እና ተግባቦት ፎረም በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፤ የኢትዮጵያን የውሃ ሀብቶች በተመለከተ ሲነገሩ የቆዩ ትርክቶችን ለመቀየር እና ሀገረቱ ከውሀ ሀብቷ የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

አሁን ላይ በዘርፉ ከ 4 የሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየተሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ጋር የመስራት ዕቅድ መኖሩን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በትብብር እየሰሩ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ እና ባህርዳር ዩኒቨርስቲ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በፎረሙ ላያ የውሃ ዘርፍ ተመራማሪዎች እየተሳተፉ ሲሆን የውሃ ሀብትን የተመለከቱ ጥናቶችም በባለሙያዎች ቀርበዋል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ