ኢትዮጵያ

ከ20 በላይ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች የስኳር ኢንተርፕራይዞችን ለመሸጥ በወጣው ጨረታ ፍላጎት አሳዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 ከ20 በላይ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች የኢትዮጵያ መንግስት 8 የስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር ባወጣው ጨረታ ፍላጎታቸውን አሳዩ።

መንግስት ባለፈው ነሐሴ ወር ስምንት የስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል።

በዚህ ሂደትም ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 2፣ ኦሞ ኩራዝ 3፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ አርጆ ዴዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ የስኳር ፋብሪካዎች ለጨረታ መቅረባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መግለጹም የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትሎም እስካሁን ድረስ 20 የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በጨረታው ፍላጎታቸውን እንዳሳዩ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ የጨረታው የእስካሁን ሂደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ጨረታው፥ ተወዳዳሪ የገበያ መዋቅር በመፍጠር የግሉ ዘርፍ በስኳር ኢንዱስትሪው ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጿል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ