ኢትዮጵያ

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የስርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የስርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 29/2015 ዓ.ም
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የስርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡

‘’የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን እና የታችኛው መዋቅር አስተዳደር’’ በሚል መሪ ቃል የ2022 የዓለም አቀፍ የረሃብ መረጃ ኢንዴክስ ሪፖርት ግብርና ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር ከአሊያንስ 2015 አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ይፋ አድርገዉ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተወያይተዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፤ የምግብና የስነ-ምግብ ፖሊሲን፣ ስትራቴጂን፣ የሰቆጣ ቃልኪዳን እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመተግበር ዜጎቹ የምግብ ዋስትና ያላቸው ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በውይይቱ አንስተዋል፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ፣ የህፃናት ሞት ለመቀነስ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የዚህ አይነት አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ መረጃዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸዉንም መግለጻቸውን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

በሀገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ዋስትናና የስርዓተ ምግብ ችግሮች ለበርካታ አመታት ያሳዩት መሻሻል በቅርብ አመታት እየቀነሰ መምጣቱን የጠቆሙት ሚኒስትሯ ይህም በነበሩት የአየር ንብረት፣ የኮቪድ፣ የዋጋ ንረት፣ ግጭትና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከመቼዉም በላይ ማህበረሰቡን ያሳተፈ በርካታ ርብርብ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

በሀገራችን ያለውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ስራ በየዘርፉ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ አጋር ድርጅቶች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከመንግስት ጋር መስራት እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ