ኢትዮጵያ

የሲንቄ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ115 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 የሲንቄ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ115 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ንዋይ መገርሳ፥ ባንኩ ላለፋት 25 አመታት በማይክሮ ፋይናንስነት በገጠር ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ሲያገለግል መቆየቱን ተናግረዋል ።

ወደ ባንክነት ካደገ 10 ወራት የተቆጠሩ ሲሆን፥ ከ7 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ይዞ ከ500 በላይ ቅርንጫፎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መክፈት መቻሉንም ነው ያመለከቱት።

ባንኩ በዛሬው እለት ከሰራተኞቹ ያሰባሰበውን 115 ሚሊየን ብር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እንዲደርስ አስረክቧል።።

ድጋፋን የተረከቡት የቦሳ ጎንፋ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮሚሽነር ሙስጠፋ አድር፥ የተደረገው ድጋፍ የተፈጠረውን ችግር በማቃለል እና እየተደረገ ያለውን የሰውና የእንስሳት ህይወት የመታደግ ስራ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

አሁንም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚው ጥሪ አቅርበዋል ።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ