ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ስምሪት አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ስምሪት አደረገ፡፡

AMN- ህዳር 17/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል በምስራቅ ኢትዮጵያ እየዘነበ ያለውን ዝናብ ተከትሎ እየተከሰተ የሚገኘውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ስምሪት አደረገ፡፡

የባህር ሀይሉ ስምሪቱን ተቀብሎ በኮሩ ማዘዣ ሲደርስ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለ ማርያምና የኮሩ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ ይመር አቀባበል አድርገውላቸውል፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አምራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለ ማርያም የነፍስ አድን ስራውን ለመስራት በቦታው የተገኙት የኢትዮጵያን ባህር ሃይል አባላት ተቀብለው በማነጋገር የጎርፍ አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለመታደግ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጣችሁ በመምጣት ለምትሰሩት ስራ መቃናት አስፈላጊውን ትብብር እናደርጋለን ብለዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ተክለ ማርያም ከመከላከያ ሰራዊታችን ተልዕኮ አንዱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ሲያጋጥም አደጋውን በመከላከል ዜጎችን የማዳን ስራ መስራት በመሆኑ በሶማሌ ክልል ሼበሌ ዞን በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የባህር ሃይሉ ሞያዊ ብቃቱን ተጠቅሞ ስራውን እንደሚሰራ እምነቴ ነው በማለት የሚሰማሩበትን ሶስት አቅጣጫ አመላክተዋል፡፡

የባህር ሀይል ትምህርትና ስልጠና ሃላፊና የቡድኑ አስተባባሪ ኮሎኔል ከበደ ሚካኤል በበኩላቸው የተሰጠን ሀገራዊ ግዳጅ ተረክበን ለመፈፀም በመጣንበት ወቅት የተደረገልን አቀባበልና አጠቃላይ ስለሁኔታው የተሰጠን ማብራሪ ስራችን ለመስራት ሁኔታዎችን በግልፅ ተረድተን ከእኛ የሚጠበቀውን ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ ማከናወን ያስችለናል ሲሉ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ