ኢትዮጵያ

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቦረና ዞን በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 የኢፌዴሪ አየር ኃይል በቦረና ዞን በድርቁ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ለዞኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

የአየር ኃይል የሰራዊት አባላት በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፉን ማሰባሰባቸውንና ለእንስሳት መኖነት በአየር ኃይሉ ግቢ ውስጥ የተመረተ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ይልማ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ከመኖው በተጨማሪ ስንዴ እንዲሁም የእንስሳት ምግብ እንደሚገኝበትና በቀጣይ አየር ኃይሉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ