ኢትዮጵያ

የክልል ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ሀገራዊ ዕቅድ አንድ ጠንካራ ብሄራዊ ሰራዊትን ዕውን የማድረግ እንጅ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ያለው አለመሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የክልል ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ሀገራዊ ዕቅድ አንድ ጠንካራ ብሄራዊ ሰራዊትን ዕውን የማድረግ እንጅ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ያለው አለመሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 29/2015 ዓ.ም
የክልል ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ሀገራዊ ዕቅድ አንድ ጠንካራ ብሄራዊ ሰራዊትን ዕውን የማድረግ እንጅ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ያለው አለመሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ደዔታ ሰላማዊት ካሳ በሰሞነኛ ሀገራዊ የፀጥታና ደህንነት እንዲሁም የልማት አጀንዳዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

መንግስት ሀገራዊ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት መቀጠሉን ያነሱት ሚኒስትር ደዔታዋ የሀገር የመጨረሻው የሉአላዊነት ምሽግ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሰው ሀይልም በአቅምም የማጎልበት ተልዕኮ ተጠናክሮ ቀጥሏልም ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም በብሄራዊ ደረጃ አንድና ወጥ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የማደራጀት ተልዕኮ በሁሉም መስክ እየተሰራበት ስለመሆኑ የጠቆሙት ሚኒስትር ደዔታዋ በክልሎች የተደራጁ የልዩ ሀይል አደረጃጀቶችን ወደ ሀገራዊ የፀጥታ መዋቀር የማስገባት በጥናትና በቅድመ ዝግጅት የተለየ እንቅስቃሴ ከጥቂት ዓመታት በፊት የታሰበ እንደነበር አውስተዋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ሲታዩ በቆዩ የሰላም መደፍረሶችና አስቻይ ያልሆኑ ሳቢያ በይደር የቆየ እንደሆነም ገልፀዋል።

አሁን ላይ እየተረጋገጠ ባለው ሀገራዊ ሰላም መነሻነት ጠንካራ የተማከለ ሰራዊት የመገንባት ተልዕኮ ዳግም ተጀምሯልም ነው ያሉት ሚኒስትር ደዔታዋ።

በዚህም በክልሎች የተደራጁ የልዩ ሀይል አደረጃጀቶችን መልሶ በዚሁ ሀገራዊ የፀጥታ መዋቅር የማደራጀት እንቅስቃሴ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ ይገኛልም ብለዋል።

የየክልል ልዩ ሀይል አደረጃጀቶች ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ ሉአላዊነትን ለማፅናት የከፈሉትን ዋጋ ሀገራዊ የፀጥታ መዋቅርን በማጠናከር ሊደግሙት እንደሚገባም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደዔታዋ ጠቁመዋል።

ይህንን የክልል ልዩ ሀይል መልሶ የማደራጀት ተልዕኮ በውል ባለመረዳት የተሳሳቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው ያሉት ሚኒስትር ደዔታዋ የክልል ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት እንቅስቃሴው ወጥና ጠንካራ ሀገራዊ የፀጥታ ሀይል የመገንባት እንጂ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ያለው አይደለም ብለዋል።

የክልል ልዩ ሀይል አባላት በሀገረ መከላከያ ሰራዊት ፣በክልል ፖሊስ አሊያም ወደ ሲቪል መካተት የሚያስችል የመልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ነውም ብለዋል ሚኒስትር ደዔታዋ።

በየትኛውም ክልል ያለው የሰላም ሁኔታ ግምገማና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ደዔታዋ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ሊያጋጥም ለሚችል የፀጥታ ስጋት የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሁሉም አካባቢዎች ስምሪት ወስዶ መንቀሳቀሱን አስታውቀዋል።

በአቡ ቻሌ

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ