ኢትዮጵያ

የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል 70 ሜትሪክ ቶን የህክምና ግብዓትና የመድኃኒት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል 70 ሜትሪክ ቶን የህክምና ግብአትና የመድኃኒት ድጋፍ ማድረጉን የድርጅቱ የሽሬ ቅርንጫፍ አስታወቀ፡፡

ድጋፉ በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና የግብዓት ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።

በድርጅቱ የሽሬ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር ቦኒፌሴ አምባኒ እንደገለጹት የጤና ተቋማትን ለማጠናከር ታሳቢ በማድረግ በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች ድጋፎች ተደርገዋል፡፡

የአሁኑ ድጋፍም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች መደበኛ የጤና አገልግሎት ለማድረስ ያለመ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ በሁሉም ኮሪደሮች ድጋፎች እየተደረጉ መሆናቸውንም ነው አስተባባሪው የተናገሩት።

የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ ሱራፌል አርዓያ በበኩላቸው÷ በአካባቢው የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ድጋፉ ለዚሁ ስራ ያግዛል ብለዋል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ