ኢትዮጵያ

የዓድዋ ድል ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 የመከላከያ ሚኒስቴር ያዘጋጀው 127ኛው የዓድዋ ድል ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ መምሪያ እየተካሄደ ነው።

የዓድዋ ድል 127ኛ ዓመት “ዓድዋ አንድነት፣ ጀግንነት እና ጽናት” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በውይይቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ጄነራል መኮንኖችና የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የታሪክ ምሁራን ተገኝተዋል።

በውይይቱ ላይ የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ ብርጋዴር ጄነራል ይታያል ገላው፣ የአድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካውያን የነፃነት ቀንዲል ነው ብለዋል።

ድሉን ተከትሎ አፍሪካውያን የፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎ ለማድረግ ወታደራዊ የሥልጠና መነሻ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ድሉ ለዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያንም የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ማስታጠቁን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን ወደ አድዋ በመትመም ጠላትን አሸንፈው ሀገራቸውን ማስከበራቸው ተገልጿል፡፡

እኛ የዚህ ዘመን ሠራዊትና ሌሎች ኢትዮጵያውንም የበለፀገችና ጠንካራዋን ኢትዮጵያ መመስረት ይኖርብናል ብለዋል ብርጋዴር ጄነራል ይታያል።

በውይይቱ ላይ የአድዋ ጦርነትና የሠራዊቱ ታሪክ እንዲሁም አድዋ የነፃነታችን መሠረትና የጥቁር ሕዝብ ኩራት በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጹሑፎች እንደሚቀርቡ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ