ኢትዮጵያ

የድንበር አካባቢ ትብብርን ማሳደግ ቀጣናውን የማስተሳሰር ውጥንን ለማሳካት ወሳኝ ሚና አለው:-አቶ አህመድ ሺዴ

የድንበር አካባቢ ትብብርን ማሳደግ ቀጣናውን የማስተሳሰር ውጥንን ለማሳካት ወሳኝ ሚና አለው:-አቶ አህመድ ሺዴ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 6/2015 ዓም

የድንበር አካባቢ ትብብር ማደግ ቀጣናውን የማስተሳሰር ሕልሞችን እውን ለማድረግ ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለው የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ።

በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ የሚገኘው የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) የፀደይ ወቅት ስብስባ ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

ከስብስባው ጎን ለጎን 16ኛው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ተነሳሽነት ‘ሆርን ኦፍ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ’ የሚኒስትሮች ስብስባ ተካሄዷል።

ኢኒሺቲቩ በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ እድገትና የልማት ፈተናዎች እንዲሁም ድህነትን ለማጥፋት የሚደረጉ ጥረቶች በተቀናጀ መልኩ ማከናወን እንዲቻል የተዘጋጀ ማዕቀፍ ነው።

የኢኒሼቲቩ ሊቀ-መንበር እና የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የድንበር አካባቢ ትብብር ማደግ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ቀጣናውን ለማስተሳሰር የያዛቸውን ሕልሞች እውን ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ የኢኒሼቲቩ አባል አገራትና አጋር ተቋማት ቀጣናዊ ትስስሩን ለማጠናከር በተቀናጀ መልኩ መስራት እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀጣናው ጥምር የጋራ የድንበር ጸጥታ ማስከበርና መሰረተ ልማት ስራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ መግለጻቸውን ዋሺንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) የፀደይ ወቅት ስብስባ ከነገ በስቲያ ይጠናቀቃል።

‘ሆርን ኦፍ አፍሪካ ኢኒሺዬቲቭ’ እ.አ.አ ጥቅምት 18/2019 የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) የፀደይ ወቅት ስብስባ ወቅት የተቋቋመ ነው።

ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያና ኤርትራ የኢኒሼቲቩ አባል አገራት ናቸው።

ቀጣናዊ ትብብር በአፍሪካ ቀንድ አገራት መካከል ያለውን የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር እንዲሁም እድገት ለማሳለጥ ያለውን ፋይዳ ከግምት ውስጥ ያስገቡ ስራዎችን እንደሚያከናውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ