ኢትዮጵያ

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

AMN- ህዳር 17/2016 ዓ.ም

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ መሆኑን የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፕሮጀክቱን አተገባበርና ዓላማ በማስመልከት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በፕሮጀክቱ የገጠር መንገድ መሠረተ-ልማትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ምቹ አጋጣሚዎች ስላሉ መሆኑ ተመልክቷል።

ለዚህም ማሳያው የገጠሩን ማኅበረሰብ ከዋና መንገድ ጋር በማገናኘት የተሻለ ህይወት እንዲኖረው በማድረግ የተገኘውን ውጤት መነሻ በማድረግ ነው።

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ ለአራት ዓመታት የሚተገበረው ፕሮጀክት የመንገድ ተደራሽነትን ከማስፋት ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጥሩ አማራጭ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ለግብርና ልማትና ምርታማነት፣ ለማዕድን ልማት እንዲሁም የግብርና ግብዓቶችን በቀላሉ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የላቀ አበርክቶ ይኖረዋል ነው ያሉት።

በፕሮጀክቱ የመንገድ ተደራሽነት በሌለባቸው አካባቢዎች የሚከናወን ሲሆን፤ በተያዘው ዕቅድ መሠረት 1 ሺህ 200 ድልድዮች የሚገነቡ ይሆናል።

በፕሮጀክቱ ምርታማነትንና የገበያ ተደራሽነትን የማስፋት ሥራም ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አመላክተዋል።

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 60 ቢሊየን ብር የሚጠይቅ ሲሆን በመንግሥትና በዓለም ባንክ እገዛ እንደሚሸፈን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ስምሪት አደረገ፡፡

admin

አስተያየት ይስጡ