ኢትዮጵያ

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ( ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም

የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስት(ኢጋድ) ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በማህበራዊ ትስስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር በድጋሚ በመገናኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል።

ኢጋድ የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና በተመለከተ እንዲሁም የኢጋድ እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በተመለከተ ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር ምክክር ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል።

ሊቀመንበሩ ባለፈው አመት በኬንያ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተገኛኝተው መወያየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

admin

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው የተለዩ 9 ዩኒቨርስቲዎችን ወደ ራስ ገዝ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው: – የትምህርት ሚኒስቴር

admin

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢክ ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን ውድድር አሸነፈ።

admin

አስተያየት ይስጡ