አለም አቀፍ

በናይጀሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቦላ ቲኑቡ ማሸነፋቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 በሣምንቱ መጨረሻ በናይጄሪያ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ቦላ ቲኑቡ አሸናፊነት መጠናቀቁ ተገለጸ።

የሀገሪቷ ገለልተኛ የምርጫ አሥፈጻሚ ኮሚሽን እንዳስታወቀው፥ የቀድሞው የሌጎስ አስተዳዳሪ ቦላ ቲኑቡ 8 ነጥብ 79 ሚሊየን ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል።

ዋና የቲኑቡ ተቀናቃኝ እና ተፎካካሪ የነበሩት አቲኩ አቡበከር ደግሞ 6 ነጥብ 98 ሚሊየን ድምፅ በማግኘት በጠባብ የድምፅ ልዩነት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ሳያሸንፉ መቅረታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

በናይጄሪያ ወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ፒተር ኦቢ 6 ነጥብ 1 ሚሊየን ድምጽ ማግኘታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቴክኖሎጂ ታግዟል የተባለውን የምርጫ ሂደት እና ውጤት አንቀበልም ማለታቸውም ተዘግቧል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

ሩሲያ የሰላም አማራጮችን እንደማትቃወም የሩሲያው ፕሬዝደንት ቪላድሚር ፑቲን አስታወቁ፡፡

admin

አስተያየት ይስጡ