
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ እና 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል።
የፕሪሚየርሊጉ ከ14ኛ እና 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አክሲዮን ማህበሩ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ በ15ኛው ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ ዝናብ ሁለት ጨዋታዎች የተቋረጡ ሲሆን ጨዋታዎቹ በመጭው ማክሰኞ እና ረቡዕ እንዲካሄዱ የአክሲዮን ማህበሩ የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
የ15ኛው ሳምንት የቀን ለውጥ የተደረገባቸውን ጨዋታዎች ተከትሎ የ16 እና 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች የጨዋታ ቀን መሻሻሉን አክሲዮን ማህበሩ አስታውቋል፡፡