
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ድል ቀንቷታል፡፡
አትሌቷ ርቀቱን በ8 ደቂቃ 16 ሰከንድ 69 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈቸው፡፡
በዚህም አትሌት ጉዳፍ አዲስ ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ 9 ሰከንድ የቀራት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ክብረወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የተያዘ መሆኑን ከወርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡