እግር ኳስ

በፕሪሚየርሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ በድጋሚ ሊጉን መምራት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ በድጋሚ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡

በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የ15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አቤል ያለው እና እስማኤል ኦሮ አጉሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ቢኒያም ጌታቸው የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተክትሎም ፈረሰኞቹ በ32 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከኢትዮጵያ መድን በድጋሚ ሲረከቡ ድሬዳዋ ከተማ በአንፃሩ በ18 ነጥቦች በነበረበት 10ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡

በጨዋታው 1 ጎል ያስቆጠረው እስማኤል ኦሮ አጉሮ በፕሪሚየርሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች 15 በማድረስ የኮከብ ጎል አግቢነት ደረጃውን መምራቱን ቀጥሏል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

admin

የፕሪሚየር ሊጉ 16ኛ እና 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የቀን ማስተካከያ ተደረገባቸው

admin

አስተያየት ይስጡ