
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 በ2023 የቶኪዮ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶች ማራቶን አትሌት ዴሶ ገልሚሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 5 ደቂቃ 22 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል፡፡
በተጨማሪም አትሌት መሀመድ ኢሳ 2ኛ እና አትሌት ጸጋዬ ከበደ ደግሞ 3ኛ በመውጣት ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሴቶች ማራቶን የተሳተፉት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ፀሓይ ገመቹ፣ አሸቴ በከሬ፣ እና ወርቅነሽ ኢዶሳ በቅደም ተከተል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል።