የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በበይነ መረብ አማካኝነት ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በበይነ መረብ አማካኝነት ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ

AMN- ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በበይነ መረብ አማካኝነት በአፍሪካ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ማሰባሰብ ጀምሯል፡፡

ትላንት በበይነ መረብ አማካኝነት በተደረገው ውይይት ከግብፅ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኬኒያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከቦስትዋና እና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አረዓያ ኮሚሽኑ እስካሁን ሰላከናወናቸው ስራዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የበይነ መረብ መድረኩ ዓላማ ከአፍሪካ ሀገራት ዲያስፖራ ማህበረሰብ አጀንዳ መቀበል እና በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ጉባኤ ተሳታፊዎችን የሚመርጡ ኮሚቴዎችን ማደራጀት እንደሆነ ያብራሩት ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ የአፍሪካ ሀገራት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአጀንዳ ሃሳቦቻቸውን በቀጥታ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ጉባኤ የሚወክሏቸውን ተወካዮች ስለሚመርጡበት ሂደት ሀሳብ እና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከተሳታፊዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኮሚሽኑ ከዳያስፓራው ማህበረሰብ በበየነ መረብ፣ በኢሜል እና በተመረጡ ሀገራት በአካል በመገኘት አጀንዳዎችን እንደሚያሰባስብ ተገልጧል፡፡

በየሃገራቱ የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በጋራ በመደራጀት ለሀገራቸው የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን እያሰባሰቡ እንዲጠብቁም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በቶለሳ መብራቴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review