የግሉ ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በተለያየ መንገድ መደገፉ ትርጉማቸው ላቅ ያለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing የግሉ ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በተለያየ መንገድ መደገፉ ትርጉማቸው ላቅ ያለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ
  • Post category:ጤና

AMN- ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች ይህንን ያሉት ሄኖክ ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የጤና ተቋማት የህክምና መሳሪያዎች እና ግብዓት ስጦታ የርክክብ ስነ ስረዓት ላይ ነው።

መሰል ትብብሮች ተጠናከረው መቀጠል አለበት፤ ትርጉሙም ብዙ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ፋውንዴሽኑ ያበረከታቸው የህክምና መሳሪያዎች አክሞ በማዳን በኩል አስተዋጽዋቸው የጎላ መሆኑን ገልጸው፣ ግብዓቶቹ በአግባቡ ይከፋፈላሉም ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የጤና አገልግሎት ተዳራሽነትን ለማስፋፋት በርካታ ሆስፒታሎችን ገንብቷል፤ እነዚህ የጤና ማዕከላት የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት ለማሟላት መንግስት ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን መሠል ድርጅቶች አበርክቷቸው ላቅ ያለ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመሆኑም ትብብሮችን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋልም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በበኩላቸው፣ በሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን የተደረገው ድጋፍ 133 የህክምና መሳሪያዎች መሆኑን ጠቁመው፣ መሣሪያዎቹ ለዘርፉ ትልቅ አቅም ይሆናሉ ብለዋል።

ድጋፎቹ በድምሩ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመቱም ገልጸዋል።

የሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን መስራች ዶክተር ንዋይ አርጋው፣ በዚህ በጎ ተግባር ውስጥ በመሳተፋቸው ላቅ ያለ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በቀጣይም በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review