የአዲስ አበባ ምክር ቤት 2ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ የተለያዩ አስፈፃሚ አካላትን ሹመቶች በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቀረበለትን የተለያዩ አስፈፃሚ አካላትና ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት
1ኛ-ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ ልትና የከተማ ውበት ቢሮ ኃላፊ
2ኛ-አቶ ቢኒያም ምክሩ
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ
3ኛ-አቶ አብርሃም ታደሰ
የአዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ
4ኛ-አቶ አደም ኑሪ
የአዲስ አበባ ከተማ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
5ኛ-አቶ በላይ ደጀን
የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
6ኛ-ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ
የአዲስ አበባ ከተማ ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ
7ኛ-አቶ ካሳሁን ጎንፋ
የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ
8ኛ-ወ/ሮ እናትአለም መለሰ
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
9ኛ-አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን
የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
10ኛ-አቶ አያሌው መላኩን
የአዲስ አበባ አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ ሰብሳቢ ሆነው በመሾም በምክርቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለመኀላ ፈፅመዋል::