አዲስ አበባ

ግብርን በመሰብሰብ ሂደት ግልጸኝነትን በመከተል ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ከግብር ሰብሳቢውና ከግብር ከፋይ አካላት የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን

ግብርን በመሰብሰብ ሂደት ግልጸኝነትን በመከተል ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ከግብር ሰብሳቢውና ከግብር ከፋይ አካላት የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መጋቢት 10/2015 ዓ.ም

ግብርን በመሰብሰብ ሂደት ግልጸኝነትን በመከተል ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ከግብር ሰብሳቢውና ከግብር ከፋይ አካላት የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

ግብር ለሀገር ክብር በተሰኘው የሽልማት እና የእውቅና መርሀ ግብር ላይ በእንግድነት ተገኙት አቶደመቀ ተሸላሚዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ አሁን ያላት አለም አቀፍ ተመራጭነትና የአፍሪካ መዲናነት እንዲጨምር እንዲሁም ለነዋሪዎቿ ምቹ ሆና እንድትቀጥል መሰረተ ልማቷን ማሳደግ በእጅጉ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በከተማዋ ደረጃቸውን የጠበቁ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶችን በማስፋፋት ረገድ ባለፉት አመታት አመርቂ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ደመቀ ነገርግን ይህ ስራ ከነዋሪው ፍላጎት እና ከአለም አቀፍ መዳረሻነቷ አንጻር ገና ብዙ መሰራት ያለባቸው ስራዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

ይህን ለማድረግ ደግሞ የከተማዋን የገቢ አቅም ማሳደግ ይገባል ያሉት አቶ ደመቀ በተለያዩ ሞያዎች ተሰማርተው የሚገኙ ነዋሪዎችም ከሚያገኙት ገቢ ላይ ትክክለኛውን ግብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አዲስ አበባ ግብር መክፈልን ግዴታቸው በማድረግ ግብራቸውን በተገቢው መንገድ የሚከፍሉ ዜጎች እንደመኖራቸው በሌላ መልኩ ተገቢውን ግብር ከመክፈል አኳያ ኃላፊነትን በግልጸኝነት አለመወጣት መኖሩን አቶ ደመቀ አውስተዋል፡፡

ግብር አሰባሰብ ስርአቱ ላይም መልካም ጅምሮች ቢኖሩም ሂደቱን ይበልጥ ማዘመንና ማስተካከል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

በግብር አሰባሰብ ሂደቱ ብርቱዎቹን ማበረታታት ጉድለት ያለባቸውን ደግሞ በማስተማር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባም አውስተዋል፡፡

ግብርን በመሰብሰብ ሂደት ግልጸኝነትን በመከተል ሃላፊነትን መወጣት ከግብር ሰብሳቢ አካላት የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም አቶ ደመቀ አንስተዋል፡፡

እንደዛሬ ተሸላሚዎች አይነት በብዙ ሺ እንዲበዙ ማበረታታት ይገባል ያሉት አቶ ደመቀ በአዲስአበባ አዳጊ የሆነውን የነዋሪውን ፍላጎት ለሟሟላት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለውን የምገባ መርሀግብር እና የኑሮ ውድነቱን የመቅረፍ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት እድሳት ፕሮግራሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ የገቢ አሰባሰብ ስርአቱን ማዘመንና ማስተካከል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮም የጀመረውን ይህን መልካም ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተመሳሳይ ልጥፎች

የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ እንዲሆንና በውይይት የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

admin

በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውሉ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ተበረከቱ

admin

የሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ፣ የቤቶችን እና የላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

admin

አስተያየት ይስጡ